በወቅታዊ የሲዳማ ዞን የፖለቲካ ኣጀንዳ፧ ሲዳማ ዞን መንግስት የሚያካህዳቸውን የልማት ስራዎች ምርጫ ተኮር ከመሆን ኣልፈው ለህዝቡ እድገት እና ብልጽግና መሆን ኣለባቸው
New Photo from Internet በሲዳማ ዞን የየወረዳ ካቢኔዎች በየወረዳው የሚገኙትን ቀበሌዎች በመከፋፈል ወቅታዊ የዞኑ መንግስት ኣጀንዳ በሆነው የግብርና ስራ ላይ ከየቀበሌዎቹ ነዋሪዎች ጋር በመምክር ላይ መሆናቸው ታውቋል። በምክክሩ ላይ ኣርሶ ኣደሮቹ በ 2006 ዓም ለማምረት እና ለመስራት በሚፈልጉትን ስራ እና ምርት በማቀድ እያንዳንዳቸው በጽሁፍ እንዲያቀርቡ በመደረግ ላይ ነው ሲሆን፤ ከዚህም ባሻገር በሌሎች ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ በኣርሶ ኣደሮቹ ለተነሱ ጥያቄዎች በካቢኔ ኣባላት ማብራርያ እየተሰጠባቸው ነው። ካቢኔዎቹ ከኣርሶ ኣደሮቹ ጋር ባደረጉት ውይይት በባለፈው ዓመት ማለትም በ 2005 ዓም የምርት ዘመን በታዩ ድክመቶችን እና ጥንካሬዎችን የመረመሩ ሲሆን፤ በዚህ ዓመት ድክመቶቹን በማረም ጥንካሬዎችን የበለጠ በማጠናከር በምቻልበት ሁኔታ ላይ ትኩረት ሰጥተዋል ተብሏል። በውይይቱ ላይ ካቢኔዎቹ እንዳሉት ከሆነ፤ የሲዳማ ኣርሶ ኣደሮች በእጃቸው ያለው ሃብት መሬት፤ የሰው ኃይል እና ውሃ በመሆኑ እነዚህን በማቀናጄት የበለጠ ምርታማነትን ማረጋገጥ ይቻላል። በምቀጥሉት የበጋ ወራት የግብርና ምርታማነትን ለማረጋገጥ በትንሽ ጊዜ ውስጥ ልደርሱ የምችሉ የግብርና ምርቶችን እንዲያመርቱ የምደረግ ሲሆን፤ ለዚህም ውሃ ከማሳቸው ኣጠገብ ያላቸው ኣርሶ ኣደሮች ከዚሁ የውሃ ሀብት እንዲጠቀሙ፧ ውሃ ከማሳቸው ኣጠገብ የሌላቸው ደግሞ የውሃ ጉርጓድ እንድቆፍሩ መክረዋል። ሪፖርተራችን ጥቻ ወራና በወቅታዊው የሲዳማ ፖለቲካ ላይ ያናገራቸው ስማቸውን እንዲገለጽ ያልፈለጉ የሲዳማ ፖለቲካ ተንታኝ የካቢኔዎቹ የልማት ዘማቻ ድብቅ ኣጀንዳ ያጋለጡ ሲሆን፤ የሲዳማን ኣርሶ ኣደሮች ምርታማነትን ለማሳደግ ካቢኔዎቹ በማድረግ ላይ ካሉት እንቅስ