ቦርዱ ለ5ኛ ጊዜ ለሚካሄደው ጠቅላላ የምርጫ አፈጻጸም የጊዜ ሰሌዳ ይፋ አደረገ

 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ5ኛ ጊዜ ለሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ አፈጻጸም የጊዜ ሰሌዳ ይፋ አደረገ።
ቦርዱ በመጪው ግንቦት ወር የሚካሄደውን አገራዊ ምርጫ  የጊዜ ሰሌዳና  ስላከናወናቸው ተግባራት ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥቷል።
የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መርጋ በቃና በዚህ ወቅት እንድተናገሩት ቦርዱ ያለፉትን አራት ምርጫዎች በመገምገምና  በቦርዱ ተመዝግበው ፍቃድ ካገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውይይት አካሂዶ ለ30 የክንውን ሂደቶች የጊዜ ሰሌዳ አውጥቷል።
በዚህ መሰረት ከህዳር 15 እስከ ህዳር 30 ፓርቲዎች የመወዳደሪያ ምልክቶች የሚመርጡበት፣ከታህሳስ 16 እስከ 27 የፖለቲካ ፓርቲዎች ዕጩ ምዝገባና ከጥር 1 እስከ 12 የመራጮች ምዝገባ የሚካሄድበት ጊዜ ይሆናል።
ከየካቲት 7 እስከ 13  ደግሞ ዕጩዎች የምርጫ ውድድር እንቅስቃሴ በይፋ የሚጀምሩበትና የሚያጠናቅቁበት፣ ግንቦት 16 የድምፅ መስጫ ቀን ሲሆን ሰኔ 15 ውጤቱ ለህዝብ ይፍ ይደረጋል ሲሉ ሰብሳቢው አብራርተዋል።
ይህ የክንውን የጊዜ ሰሌዳ የተለየው በአዲስ አበባ ካሉት 23 የፖለቲካ ፓርቲዎች ከ22ና በክልሎች ከሚገኙ ፓርቲዎች ጋር በአዳማና በሃዋሳ ከተማ ዝርዝር ውይይቶች ከተደረገ በኋላ እንደሆነ አስረድተዋል።
ከፓርቲዎቹ ጋር በተደረገው ውይይት የዕጩዎችና የመራጮች ምዝገባ እንዲራዘም ለቀረበው ጥያቄ ስምምነት ላይ ተደርሷል።
ቦርዱ ምርጫው የተሳካ እንዲሆን የ2002 ጠቅላላ ምርጫን ከሚመለከታቻው  ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ሰፊ ሳይንሳዊ ጥናት አካሂዶ የጥናቱን ወጤት ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት አሰራጭቷል።
ከጥናቱ በኋላ የቦርዱ የትኩረት አቅጣጫንና የአምስት አመቱን የእቅድና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ መሰረት በማድረግ ከፍተኛ እንቅስቃሴ አድርጓል ብለዋል።
በዚህም ቦርድ በሰው ሃይል አሰላለፍ፣አስፈላጊውን የምርጫ ቁሳቁስና ኮሮጆ ዝግጅት 90 በመቶ አጠናቋል።
በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ በምርጫ ቦርድ ህጋዊ እውቅና አግኝተው የሚንቀሳቀሱ 75 የፖለቲካ ፓርቲዎች አሉ።
Source: www.ena.gov.et

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር