በ6ኛው የከተሞች ፎረም ውድድር የሲዳማዋ መዲና ሃዋሳ ከተማ አሸናፊ ሆነች

በ6ኛው የከተሞች ፎረም ውድድር የሲዳማዋ መዲና ሃዋሳ ከተማ አሸናፊ ሆነች። ዝርዝር ወሬውን ከታች ያንቡ፦

ባለፉት አመታት በከተማ ልማት ዘርፍ የተሸለ ስራ መስራቱን የከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚንስቴር ገለፀ፡፡
“ከተሞቻችን የኢንተርፕራይዞች ልማት ማዕከላት በመሆን የኢትዮጵያን ህዳሴ ያሳካሉ” በሚል መሪቃል በድሬዳዋ ሲካሄድ የሰነበተው የከተሞች ፎረም ተጠናቋል፡፡
በመዝጊያው ላይ ንግግር ያደረጉት የከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚንስትሩ አቶ መኩሪያ ሃይሌ እንዳሉት፥ ባላፉት አመታት በከተማ ልማት ዘርፍ የማስፈጸም አቅም በመጠናከሩ የተሸለ ስራ መስራት ተችሏል፡፡
በጥቃቅንና አነስተኛ ለ3 ሚሊዮን ሰዎች የስራ ዕድል ለመፍጠር ታስቦ እየተሰራ መሆኑን የገለፁት ሚኒስትሩ ለማምረቻ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ትኩረት እንደተሰጠ ገልጸዋል፡፡
በጠቅላይ ሚንስትር ማዕረግ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪና የመገናኛ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚንስትር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል በበኩላቸው ከተሞች የሀገሪቱ የዕድገት አውታር መሆናቸውን ጠቁመው፥ ከተሞች በተፋጠነ መልኩ እድገታቸው እንዲቀጥል የከተማ አጀንዳዎችን ከኪራይ ሰብሳቢነት የማጽዳት ስራ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል፡፡
የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አሰድ ዚያድ በበኩላቸው፥ ከዝግጅቱ መልካም ልምዶችን እናዳገኙ ተናግረዋል፡፡
ልምዱን ተጠቅመውም የከተማቸወን ዕድገት እንደሚያፋጥኑ ገልፀዋል፡፡
189 ከተሞችንና ባለድርሻ አካላት በተሳተፉበት መድረክ ለሞዴል ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተፕራይዞች፣ ለሴት ኢንተርፕረነሮች እንዲሁም ወደ ታዳጊና መካከለኛ ለተሸጋገሩ ኢንተርፕራይዞች እውቅና ተስጥቷል፡፡
ከተሞች በፎረሙ ላይ ራሳቸውን ለማስተዋወቅ ባደረጉት ውድድር በምድብ አንድ የሃዋሳ ከተማ አሸናፊ ስትሆን፥ አዲስ አበባ ከተማ ልዩ ተሸላሚ ሆናለች፡፡
በቀጣይነት የከተሞች ፎረም በየሁለት አመቱ የሚካሄድ ሲሆን በ2009 የጎንደር ከተማ እንድታዘጋጅ ተመርጣለች፡፡
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር