በጀርመኗ ኮሎን ከተማ በተከፈተው ኣለም ኣቀፍ የፋይን ኣርት ኤግዚብዥን የሲዳማ ባህላዊ ''Barikko'' ባርኮ ለእይታ ቀረበ


የኮሎን ከተማ ለኣለም የጥበብ ሪዕዬ ትይዕንት ሰሞኑን በሯን ክፍት ኣድርጋ ከተለያዩ የኣለም ክፍሎች የምጎርፉትን ጥንታዊ እና ባህላዊ የጥበብ ስራዎች በመቀበል ላይ ትገኛለች።

በሪዕዬ ትይእንቱ ላይ ዘመን ጠገብ ቁሳቁሶች ለእይታ የቀረቡ ሲሆን፤ ከቀረቡ ቁሳቁሶች መካከል በ19ኛው እና በ20ኛው ክፍለ ዘመን የተፈበረኩ እና በህዝብ ዘንድ ተወዳጅነትን ያተረፉ መኪኖች እና የስዕል ስራዎች ይገኙበታል።

ለኣብነት ያህል ከቀረቡት የስዕል ስራዎች መካከል በጀመናዊው የኤክፕሬሽን ሰዓል ኣርቲስት ማክስ ፔሄስታይን የተሳሉት ሁለት ስዕሎች በሽያጭ የቀረቡ ሲሆን ዋጋቸውም 1 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዬሮ መሆኑ ታውቋል።



የወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ ዘጋብ የዩሮ ኒውስን ጠቅሶ እንደዘገባው፤ በኣማካይ 100 የምሆኑ ጋሌሪዎች እና ደላሎች ከኣውሮፓ እና ከተቀረው ኣለም ሃሰባሰቧቸው ማስተርፒስ ስራዎች በተጨማሪ ከኢትዮጵያን እና ኬኒያ የተሰባሰቡ ባህላዊ ቁሳቁሶች ለእይታ የቀረቡ ሲሆን የሲዳማው ባርኮ ከእነዚሁ መካከል ኣንዱ ነው።


Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር