ፊቼ ጨምበላላ የመላ ኢትዮጵያውያን ኩራትና የአለም ቅርስ በመሆኑ ተገቢው ጥበቃ ሊደረግለት ይገባል-ፕሬዚዳንት ሙላቱ

ፊቼ ጨምበላላ የመላ ኢትዮጵያውያን ኩራትና የአለም ቅርስ በመሆኑ ተገቢው ጥበቃ ሊደረግለት ይገባል-ፕሬዚዳንት ሙላቱ

(ኤፍ.ቢ.ሲ) የፊቼ ጨምበላላ የሲዳማ ብሄር የዘመን መለወጫ በዓል የመላ ኢትዮጵያውያን ኩራትና የአለም ህዝብም ቅርስ በመሆኑ ተገቢው ጥበቃ ሊደረግለት እንደሚገባ ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ አሳሰቡ።
የፊቼ ጨምበላላ ዘመን መለወጫ በዓል ዋዜማ በሀዋሳ ከተማ በተለያዩ ስነሰርዓቶች እየተከበረ ነው።
በዓሉ ከአሮጌ ዓመት ወደ አዲስ ዓመት መሸጋገርን ለማሳየት የሚከበር ነው።
የዘንድሮው በዓል የማይዳሰስ ዓለም አቀፍ ቅርስ ሆኖ በዩኔስኮ በተመዘገበ ማግስት፥ ለመጀመሪያ ጊዜ በሃገር አቀፍ ደረጃ የሚከበር መሆኑ የተለየ ያደርገዋል ተብሏል።
በዛሬው እለትም የሲዳማ ባህል ፓርክ ግንባታ ማስመጀመሪያ የመሰረት ድንጋይ የማስቀመጥ ስነ ስርዓት በጉዱ ማሌ አደባበይ ተከናውኗል።
የመሰረት ድንጋዩን ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ በዛሬው ዕለት አስቀምጠዋል።
በዚሁ ወቅት ፕሬዚዳንቱ እንዳሉት፥ የማእከሉ መገንባት የሲዳማን ባህልና ማንነት ከማስተዋወቅ በላይ የመላ ኢትዮጵያውያን ሀብት እንዲሆን ያስችለዋል።
ማእከሉ በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅም የሚመለከተው አካል ሁሉ በትኩረት እንዲንቀሳቀስ ፕሬዚዳንቱ ጠይቀዋል።
ከ1 ቢሊየን በላይ ወጪ የሚደረግበት ማዕከሉ በአራት አመታት ውስጥ ተገንብቶ እንደሚጠናቀቅም ነው የተመለከተው ።
ማዕከሉ በውስጡ ሙዚየሞች፣ የተለያዩ ማዕከላት፣ ካፍቴሪያዎች፣ የመዝናኛ ቦታዎች፣ ጥብቅ ደንና ሌሎችም በርካታ ክፍሎችን ያካተተ ነው።
በስነስርዓቱ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደሴ ዳልኬን ጨምሮ ከፍተኛ የክልሉ የስራ ሃላፊዎች፣ ከዩኒስኮ የተወከሉ የስራ ሃላፊዎች፣ በ100 ሺህ የሚቆጠሩ የሲዳማና የአካባቢው ህዝቦች ተሳታፊ ሆነዋል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር