Posts

ከእኛ ዞንስ ምን ታስቧል?

Image
በትግራይ የንግድ ታፔላ ማስታወቂያዎች በትግርኛ እንዲፃፉ ተደነገገ ‹‹የክልሉን ቋንቋ ለማሳደግ አስተዋፅኦ ያበረክታል›› ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ የስራ ቋንቋውን ትግርኛ ያደረገው የትግራይ ክልላዊ መንግስት፤ ማንኛውም የንግድ ማስታወቂያ ታፔላና የግድግዳ ላይ ማስታወቂያ መልዕክቶች በትግርኛ ቋንቋ እንዲፃፉ የሚያዝ አስገዳጅ አዋጅ ሰሞኑን አፀድቆ በስራ ላይ መዋል መጀመሩ ተገለፀ፡፡ አዋጁን እንዲያስፈፅም ኃላፊነት የተሰጠው የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ኃይሉ ለአዲስ አድማስ በሰጡት ማብራሪያ፤ አዋጁ ማንኛውም የንግድ ድርጅትም ሆነ አገልግሎት ሰጪ ተቋም፤ የውጪ ተሰቃይ ማስታወቂያውን ወደ ትግርኛ  እንዲለውጥ የሚያስገድድ መሆኑን ጠቁመው፤ አዋጁን ተግባራዊ ያላደረገ ድርጅቱ እንደሚታሸግበት ያሳስባል ብለዋል፡፡  ቀደም ሲል እንዲህ ያለው አስገዳጅ ህግ ባለመኖሩ፣ በክልሉ ከተሞች የሚሰቀሉ የግድግዳ ላይ ማስታወቂያዎችና ታፔላዎች  የተዘበራረቀ ቋንቋ ይጠቀሙ እንደነበር የጠቀሱት አቶ ዳዊት፤ ይህን የሚያስቀር አዋጅ መፅደቁ ለክልሉ ቋንቋዎች እድገት አስተዋፅኦ ያበረክታል ብለዋል። በክልሉ የራሳቸውን ቋንቋ የመጠቀም ህጋዊ መብት የተሰጣቸው የሳኦና የኩናማ ብሄረሰቦችም በከተማ ውና አካባቢያቸው፣ ማናቸውም የግድግዳ ላይ ማስታወቂያዎችና ታፔላዎች በየራሳቸው ቋንቋ እንዲፃፉ አዋጁ ያስገድዳል ተብሏል፡፡   አዋጁ ገና በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ እንዳልወጣ የተጠቆመ ሲሆን የመቀሌ ከተማ አብዛኞቹ የንግድ ቤቶችና ተቋማት አዋጁ መውጣቱን ተከትሎ ታፔላቸውን ወደ ትግርኛ ቋንቋ በመቀየር ተጠምደው መሰንበታቸውን ከአካባቢው ምንጮቻችን  ለማወቅ ተችሏል፡፡ የቢሮ ኃላፊው አቶ ዳዊት በበኩላቸው፤ በእርግጥም ታፔላዎች ከወዲሁ እየተቀየሩ መሆኑንና የህብረተሰቡ ተግባ

Hawassa University (HU) Documentary 2017 in Sidaamu Afoo

Image
Hawassa University Documentary- 2017- Sidaamu Afoo